እንኳን ለ2006 ዓ.ም ጾመ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹ወዘሰ እንተ አንቀጽ ይበውእ ኖላዌ ዓባግዕ ውእቱ ፤

በበሩ የሚገባ የበጎች እረኛ ነው›› (ዮሐ 10 ÷ 2)

በብሉይ ኪዳን የበጎች እውነተኛ እረኛ እንደሆነ በብዙ ስፍራ የተነገረለት መሢሕ አንድ ቀን በዓለም እንደሚገለጽና በጎቹን በትክክል እንደሚጠብቅ በሕዝበ እግዚአብሔር ዘንድ የታወቀና የታመነ ነበረ (ሕዝ 34 ÷ 1-24) ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ በተለያዪ አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ ቆይቶ የሚቀጥለውን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ፡፡

ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ በኃይለ መለኮቱ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንንም በልዩ አጠራሩ ጠርቶ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በሚካሄደው በዚህ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፡፡

“ወንሩጽ በትዕግሥት ኀበ ዘጽኑሕ ለነ ተስፋነ ዘሃይማኖት፣ ተጠብቆልን ወዳለ ተስፋ ሃይማኖት ለመድረስ በትዕግሥት እንሩጥ” ዕብ. 12፡1

ርክበ ካህናት ተብሎ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሚታወቀው፣ ከጌታችን በዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን፣ ማለትም በመንፈቀ በዓለ ሐምሣ በየዓመቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲደረግ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትደነግግ ትልቅ ዓላማ አላት፤

የጉባኤው ዓላማ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከመንፈስ ቅዱስ በተሰጣቸው ሐዋርያዊ ተልእኮ መሠረት በየተመደቡበት ሀገረ ስብከት ሲሠሩ በመንፈሳዊም ሆነ በአስተዳደራዊ ሥራቸው ያጋጠመ እክል ካለ በጋራ ተሰብስበው ችግሩን መፍታት የሚያስችል ጥበብ እንዲፈልጉለት ለማድረግ ነው፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የቅዱስ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በጎንደር ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡

ክፍል 1
ክፍል 2
ክፍል 3
ክፍል 4
ክፍል 5

ከሀገር ወጥቶ የቆየው የመድኃኔ ዓለም ታቦት ወደ ሀገሩ ተመለሰ::

ታቦቱ አዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ምእመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ባልታወቀ ምክንያት ከቤተክርስቲያኒቱ የሸዋ ሃገረ ስብከት ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የጠፋው ይህ ታቦት በግለሰቦች ጥቆማ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ትብብር ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ ችሏል።

ጽላቱ በመንበረ ፓትርያርክ በተደረገለት አቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ የጅቡቲ ምስራቅ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ዮናስ መልከ ጸዴቅ ከሀገር እንዴት እንደወጣ በውል ያልታወቀው ይህ ጽላት የተገኘው በአንድ ጅቡቲያዊ ቤት መሆኑን ተናግረዋል።

ለሙሉ ንባብ እንዲሁም ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ

‹‹ወርኢናሃ ለሕይወት፤ ወተዐውት ለነ፤ ሕይወትን አየናት፤ አወቅናትም›› (1ዮሐ 1፡2)

የሕይወት መገኛና ምንጭ አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የተገኘው ሕይወት የሰው ልጅ የዕውቀት ብርሃን ነው፤ አምላካዊ ሕይወት ካለው ሰው የሚፈልቅ ብርሃናዊ ዕውቀት ጽልመታዊውን ዓለም በብሩህነቱ ያሸንፋል እንጂ በጽልመታዊ ዓለም አይሸነፍም፡፡ (ዮሐ. 1፡4-5)

ሰው ከእግዚአብሔር በተሰጠው ነጻነትና አእምሮ መሠረት ነጻነቱን ተጠቅሞ የመረጠውን የማድረግ ነጻነት ያለው ፍጡር ቢሆንም በነጻ ዕውቀቱና ምርጫው ለሚፈጽመው ሁሉ እርሱ ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

ይህም ማለት በምርጫው መሠረት የሚሠራውሥራ ሁሉ በእውነተኛው ዳኛ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ሆኖ ከተገኘ ምስጋናን፤ መልካም ሆኖ ካልተገኘ ግን ተጠያቂነትንና ፍርድን ያስተከትልበታል ማለት ነው፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡ ወይም ከዚህ በታች በቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

የጸሎተ ሐሙስ፤ የስቅለት፤ የቀዳም ስኡርና የትንሳኤን በዓል አከባበር ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡

‹‹እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፤ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር …››

ሁላችንንም በዚህ ታሪካዊ ዐውደ ምሕረት ሰብስቦ ስሙን በመጥራት ስሙን በመቀደስ፤ ቃሉን በመስማት፤ ይህን በየዓመቱ መጋቢት 27 ቀን የሚውለውን የ2006 ዓ.ም ዓመታዊ በዐል ለማክበር ላበቃን እግዚአብሔር አምላካችን ክብር ምስጋና ይግባው፡፡

‹እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ በማዕከለ ምድር ቀራንዮ ኢየሩሳሌም ተሰቅሎ ባፈሰሰው ደሙ መድኃኒትን አደረገ› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 73፡12)

ይህ በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት የምናከብረው በዐላችን ዓመተ ፍዳው፣ ዓመተ ኵነኔው አክትሞ የሰው ዘር የሆነው ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከኃጢአት ወደ ስርየት፤ ከሲኦል ወደገነት፤ የተመለሰበትና የተሸጋገረበት ዕለት መሆኑን ለማዘከር ነው ::

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ እየተባሉ የሚጠሩት ግለሰብ የሚያደርጉትን የማታለልና የማጭበርበር ተግባር እንዳይፈጽሙ ታገዱ፡፡

ግለሰቡ የሚያደርጉትን የማታለልና የማጭበርበር ተግባር እንዳይፈጽሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታገዱ ሲሆን የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ታደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን በጥብቅ ታሳስባለች፡፡

የእገዳ ድብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ቶማስ አረፉ፡፡

በጎጃም ጠ/ግዛት በቆላ ደጋ ዳሞት አውራጃ በደጋ ዳሞት ወረዳ በመንበረ ስብሐት ዝቋላ አርባእቱ እንስሳ ቀ/ገበሬ ማህበር ውስጥ ከአባታቸው ብላታ ተገኘ ይልማ ገ/ሕይወት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ውድነሽ ቸሬ መጋቢት 14 ቀን 1935 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ‹‹ዘእንበለ እፍጥርከ አእመርኩከ ወዘንበለ ትጻእ እምከርሠ እምከ ቀደስኩከ ወረሰይኩከ መምህረ ለአህዛብ›› ተብሎ ለነብዩ ኤርሚያስ እንደተነገረለት ኤር 1.4 ብፁዕ አባታችን በብጽዓትና በፈቃደ አምላክ የተገኙ ማህደረ መንፈስ ቅዱስ በመሆናቸው በወላጆቻቸው ቤት ወልህቀ በበህቅ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ ሉቃስ 2.51 እንደተባለው ለወላጆቻቸው በመታዘዝና በማገልገል ካደጉ በኋላ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በተወለዱ በ7 ዓመታቸው በደጋ ዳሞት ወረዳ ጉድባ ቅ/ማርያም ከሚገኙበት ከታላቁ ሊቅ መምህር አንዱ ዓለም አስረስ ከመልክዐ ፊደል ጀምሮ ፀዋትወ ዜማን ተምረዋል፡፡

የብፁዕ አባታችንን ሙሉ ዜና ዕረፍትና የሕይወት ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ" በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡

ከዚህ በታች ያሉትን በመጫን ትክክለኛውን እና ሐሰተኛውን ደብዳቤ እንድታነቡና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡

ትክክለኛውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡ ለማጭበርበር የተበተነውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ በዓለ ሲመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የመላ አዲስ አበባ ካህናትና ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ፡፡

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

‹‹ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽላዓ ለነፍሱ፣ሊከተለኝ የሚወድ ራሱን ይካድ›› ማቴ.16÷24፣

ጌታችንን ይከተሉ የነበሩ ሐዋርያት በመጀመሪያዎቹ የትምህርተ ወንጌል ዓመታት የነበራቸው አስተሳሰብ ወደ ፍቅረ ሢመትና ወደ ፍቅረ ንዋይ ያደላ እንደነበረ ቅዱስ ወንጌል ያመለክታል፤ የያዕቆብና የዮሐንስ እናት ‹‹እነዚህ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱ ደግሞ በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ›› (ማቴ.20÷21) ማለቷ በእሥራኤል አስተሳሰብ መሢሑ ይነግሣል፣ ሮማውያንንም ከእሥራኤል ምድር ያስወግዳል፣ በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው የእሥራኤል ኃያል መንግሥትን አቋቁሞ መላ ዓለምን በጽድቅ ይገዛል፤ የሚለውን የአይሁድ አስተሳሰብ በመከተል መንገሡ አይቀርምና በነገሠ ጊዜ ልጆቿን አንዱን ቀኛዝማች ሌላኛውን ግራዝማች ብሎ እንዲሾምላት ካላት ፍላጎት የመነጨ ሐሳብ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሁለቱ ልጆችዋም ከእርስዋ ጋር አብረው መቅረባቸው ይህንን አምነውበት ምላሹን ለመስማት እንደነበረ አይጠረጠርም፡፡

ለሙሉ ንባብ እንዲሁም በቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቢይ ጾምን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ፡-

እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስድስት ዓመተ ምሕረት የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹‹ወእመሰ በምግባረ መንፈስ ቀተልክምዎ ለምግባረ ነፍስትክሙ ተሐይዉ ለዓለም፤ በመንፈሳዊ ሥራ ሥጋዊ ሥራችሁን ብትገድሉ ለዘላለሙ ትድናላችሁ›› (ሮሜ.8÷13)፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡ እንዲሁም ለወቅታዊ ክንውኖች እዚህ በመጫን ያንብቡ፡፡

በአክሱም ጽዮን የፅላተ-ሙሴ ጊዜያዊ ማቆያ ቤተ መቅደስ ተመረቀ ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ጠብቀውና ተንከባክበው ያቆዩልንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶቻችንን በሚገባ መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ፅላተ-ሙሴ ለዘመናት ያረፈችበትን ቤተ መቅደስ ለማደስ ሲባል በጊዜያዊነት ፅላቷ የምታርፍበት ቤተ መቅደስ ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት አባቶቻችን ተንከባክበው ያስረከቡንን እምነታችንና መንፈሳዊ ቅርሶቻችንን ኢትዮጵያ አገራችን በዓለም በከፍተኛ ደረጃ እንድትታወቅ አድርገዋታል ብለዋል፡፡

ለሙሉ ንባብ እንዲሁም በቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የ2006 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ፡፡

"ወለደነ ዳግመ በጥምቀቱ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባላት፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች እንሆን ዘንድ በጥምቀቱ ዳግመኛ ወለደን"(1 ጴጥ. 5፣ ዮሐ. 3፣5-7)፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ሰውን በአርአያውና በመልኩ መፍጠሩ ሰው በክብር ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የሆነ ክብር ያለው መሆኑን ለመግለጽ እንደሆነ መገንዘቡ አያስቸግርም፡፡

ሰው በተፈጥሮው በሰማይም ሆነ በምድር ካሉ ፍጥረታት ሁሉ በተለየ ሁኔታ እንደተፈጠረ በቅዱስ መጽሐፍ ግልጽ ሆኖ ተጽፎአል፤ ይኸውም በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠሩ፣ ከምድር አፈር ከተፈጠረ በኋላ በአፍንጫው የሕይወት መንፈስ ከእግዚአብሔ መቀበሉ፣ በፍጥረታት ላይ ገዥ ሆኖ መሾሙና መባረኩ፣ ከሌሎች ፍጥረታት የተለየና የከበረ መሆኑን ያስረዳል፤ (ዘፍ. 1፡26-28 ዘፍ. 2፡7)፡፡

ሰው በተፈጠረበት አኳኋን የተፈጠረ ሌላ ፍጥረት ስለመኖሩ፣ ቅዱስ መጽሐፍ አይገልጽም፤ በመሆኑም ሰው የፍጥረታት ጌታ፣ የፍጡራን ሁሉ ጌጥ፣ የእግዚአብሔር ባህርይ መገለጫ በመሆኑ፣ ክብሩ ከሁሉም ፍጥረታት በላይ ነው ፡፡

ለሙሉ ንባብ እንዲሁም ለምስልና ቪዲዮ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የ2006 ዓ.ም የልደት በዓልን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ፡፡

“ወናሁ ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰምዪዮ ስሞ ኢየሱስ ዘውእቱ ያድኅኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ፤ እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ” (ሉቃ 1፤ 31 ማቴ 1፡21)፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁእ አቡነ ገሪማ የጻድቁን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓል አስመልክተው መልዕክት አስተላላፉ፡፡

‹‹ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ››

‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 111፡6)

ከዚህም ጋር ‹‹አፋሁ ለጻድቅ ይትሜሐር ጥበበ፤ ወልሳኑ ይሰብብ ጽድቅ፤ ወሕገ አምላኩ ውስተ ልቡ››

‹የጻድቅ አፉ ጥበብን ይማራል፤ አንደበቱም ጽድቅን ይናገራል፤ የአምላኩም ሕግ በልቡ ውስጥ ነው› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 36፡30)

ይህ የቅዱሳን አበው ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታት ቋሚ መታሰቢያ፤ ሕገ እግዚአብሔርን ለማክበር፣ ለማስከበር፣ ከልደት እስከ ዕረፍት የሆነውን የተቀበሉትን መከራ፣ የፈጸሙትን ተጋድሎ አጠቃሎ የሚያስረዳ መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡

ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ እዚህ በመጫን የዩኔስኮ ድረ ገጽን ይመልከቱ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሁለት ሚሊዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ ለማድረግ ወሰነች ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቀጣይም ቤተ ክርስቲያኗ ርዳታዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል ፡፡

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ በመንበረ ፓትርያርክ አዳራሽ በተደረገው አስቸኳይ ጥሪ እንደተገለፀው ቤተ ክርስቲያኗ ቀደም ሲል በገባችው ቃል መሠረት ለጊዜው የሁለት ሚሊዮን ብር ርዳታ ታደርጋለች ፡፡ ገንዘቡም የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ለሚመለከተው አካል ገቢ ይደረጋል ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ሁላችንንም በዚህ ታሪካዊ ቅዱስ ቦታ ሰብስቦ ስሙን በመጥራት፣ ስሙን በመቀደስ፣ ቃሉን በመስማት ይህን ዓመታዊውን በዐላችንን ለማክበር ያበቃን እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡

‹‹ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ፤ ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ፤ ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ፣ ወትትካፈልዎ፣ ለክበዲሃ፣ ከመ ትንግሩ ለካልእ ትውልድ፤ ከመ ዝንቱ ውእቱ አምላክነ፣ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፣ ወውእቱ ይርዕየነ እስከ ለዓለም››

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በተለያዩ ምክንያቶች ከአገር ወጥተው በስደት የሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሃይማኖትና ፖለቲካ ሳይለያያቸው በአገር ጉዳይ በጋራ እንዲሠሩ አሳሰቡ፡፡

ቅዱስነታቸው በአሜሪካ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ከበርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያት ጋር ውይይት አካሒደዋል ፡፡

ተጨማሪ ፎቶዎችን እዚህ በመጫን ይመልከቱ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በዓለም ላይ የፖለቲካና የሃይማኖት ልዩነት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው በአሜሪካ በተለያዩ ክፍላተ ሀገር በመዘዋወር ስለ አንድነት፣ ሰላምና ትብብር ኢትዮጵያውያኑ ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ ወቅዱ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በጎጃም ደብረ ወርቅ እና መርጡ ለማርያም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ::

ተጨማሪ ቪዲዮዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

መደበኛ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ተፈፀመ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባን በማካሔድ፤

- ለቤተ ክርስቲያናችንና ለኅብረተሰቡ የሚጠቅመውን፤

- ለሀገርና ለዓለም ሰላም የሚበጀውን አጀንዳ በማመቻቸት በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፤

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

መደበኛ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ተጀመረ፡፡

የዛሬው ጉባኤያችን፣ በፍትሕ መንፈሳዊ በተደነገገው መሠረት፣ ወቅታዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮችን በማንሣት ለመወያየትና፣ መንፈስ ቅዱስ በሚገልጽልን መንፈሳዊ ጥበብ እየተመራን፣ መፍትሔ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች፣ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሆነ ሁላችሁም ታውቃላችሁ ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣ በአሁኑ ጊዜ በጥልቀት፣ በማስተዋልና የኃላፊነት መንፈስ በተላበሰ ወኔ፣ አጥብቆ ሊወያይባቸውና ሊወስንባቸው፣ ከውሳኔ በኋላም ለተግባራዊነታቸው ሊረባረብባቸው የሚገቡ፣ በርከት ያሉ ጉዳዮች እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 32ኛው መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ፡፡

ክፍል 1

ክፍል 2

ክፍል 3

ክፍል 4

ብፁእ አቡነ ገሪማ ሊቀ ጳጳስ ዶክተር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ2006 ዓመተ ምሕረት በዐለ ቅድስት ድንግል ማርያም ወበዐለ መስቀሉን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የዘመናት ባለቤት፤ ዓመታት የማይወስኑት፤ ዘመን የማይቆጠርለት፤ ዘመናትን በዘመን እያደሰ ፍጥረታትን ሲመግብ የሚኖር፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ለዚህ ዕለትና ሰዓት አድርሶ፤ በዚህ ዐውደ ምሕረት ሰብስቦ፤ ስሙን በመጥራት፤ ስሙን በመቀደስ፤ ቃሉን በመስማት የ2006 ዓመተ ምሕረት በዐለ ቅድስት ድንግል ማርያም ወበዐለ መስቀሉን ለማክበር ላበቃን እግዚአብሔር አምላካችን <<ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ለዘኣብጽሐነ፤ እሰከ ዛቲ ሰዓት>> በማለት እናመሰግነዋለን:: (ሉቃስ 2፡14)

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሁኖ ‹‹ወይቤ ተፈጸመ ኩሉ›› ‹ሁሉም ነገር ተፈጸመ፤ አለቀ ደቀቀ› ከማለቱ በፊት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም፣ የእናቱም እኅት፣ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፤ መግደላዊት ማርያምም በጌታችን በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አጠገብ ቆመው ነበር፤ ይላል ቅዱስ ወንጌል (ዮሐ. 19፡25)

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመስቀል በዓልን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ በረከት

በቅዱስ ደሙ ፈሳሽነት ከኃጢአት፣ ከሞተ ነፍስና ከሲኦል ግዞት ነጻ አድርጎ ያዳነን ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!

‹‹መስቀል ዓለም የዳነበት የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ነው››፤ (1ቆሮ.1÷18-24)

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በመላ ኢትዮጵያና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡-

እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን፣ መስቀልን በታላቅ ድምቀት የምናከብርበት ዋናው ምክንያት፤ መስቀል ሰዎችን ለድኅነት፣ ዲያብሎስን ለሽንፈት ያበቃ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ በመሆኑ ነው፤

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የ2006 ዓ.ም የተቀፀል ጽጌ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከበረ፡፡

በየዓመቱ መስከረም 10 ቀን በድምቀት የሚከበረው የተቀፀል ጽጌ በዓል በዘንድሮውም ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት በሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ

ሙሉ መርሃ ግብሩን በቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት

ሙሉ መርሃ ግብሩን በቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

የ2006 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል መሰብሰቢያ አዳራሽ የእንኳን አደረሳችሁ ፕሮግራም ተካሔደ፡፡

ሙሉ መርሃ ግብሩን በቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2006 ዓ.ም መግባትን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

የዘመናት ፈጣሪ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ከሁለት ሺ አምስት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ወደ ሁለት ሺሕ ስድሰት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማርቆስ በሰላም አደረሳችሁ!!!

“ወሠርዐ ዕድሜሁ ወዓመታቲሁ መጠነ ይነብሩ በዘየኃሥሥዎ ለእግዚአብሔር፤ እግዚአበሔር፣ እርሱን ፈልገው ያገኙት ዘንድ፣ ሰዎች የሚኖሩባቸውን የዕድሜና የዘመናት መጠን ሠራ” (የሐ.ሥራ.17÷26-27)

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ለምእመናንና ለህፃናት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋት ትምህርት ተሰጠ ፡፡

ሙሉ መርሃ ግብሩን በቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተሰራው ዘመናዊ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ::

ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ፡፡ ፎቶ ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የሰላም የጋራ ጉባዔ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ተካሔደ፡፡

ሃይማኖት ያለው ሕዝብ ሁሉም ሰላም ከእግዚአብሔር እንደሆነ ያውቃል ፡፡ ሰላም ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጠ ጸጋ መሆኑንም ይገነዘባል ፡፡ ለሰላምም በርትቶ ይቆማል፡፡ ሰላም በባሕርዩ የሰላም አምላክ ከሆነው ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ቅዱስ ስጦታ ስለሆነ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዘዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል›› ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ጸንቶ ይኑር›› ይላሉ (መዝ. 28፡11፣ ቆላስ 3፡15) የሃይማኖት ዋነኛ ተልዕኮ በሰው ልጆች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ነው በማለት ተናግረውታል ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃለ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእንተ ጸሎት ዘተገብረ ለዓቢይ መራሒ ዘኢትዮጵያ ዘውእቱ መለስ ዜናዊ

በዛሬው ዕለት በዚህ ካቴድራል የተሰበሰብንበት ዓቢይ ጉዳይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የክቡር መለስ ዜናዊ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ ማርያም ኣመታዊ የመታሰቡያ ጸሎት ለማድረስ ነው፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

እንኳን ለበዐለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ፡፡

‹በረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዐላችን ዕለት፣ መለከትን ንፉ፤ የቤተ እስራኤል ሥርዓት ነውና› ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት (መዝ. 80፡1-4)

በዚህ መዝሙረ ዲዊት መነሻነት ከዚህ በሊይ በተነገረው መዝሙረ ዲዊት መሠረት ይህን በዏሇ ዯብረ ታቦር በዏሊችንን በየገዲማቱና አዴባራቱ በየገጠሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ ነሏሴ 13 ቀን በታሊቅ ሥነ ሥርዓት እናከብረዋሇን፡፡

ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

‹‹ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ››

ከማናቸውም ክፉ ነገር የራቁ፤ እግዚአብሔርን ያወቁ፣ ሕጉን የጠበቁ፣ ስሙን የሚጠሩ፣ የሚቀድሱ ከብፅዕና፣ ከቅድስና ደረጃ የደረሱ ብፁዓን ኤጲስ ቆጶሳት፣ ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳትና ፓትርያርኮች ብፁዓን ቅዱሳን ተብለው እንደሚጠሩ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል ፡፡ ‹‹ኩኑ ቅዱሳነ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ›› ‹እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ› ይላል የእግዚአብሔር ቃል ፡፡ (ዘሌዋ. 19፡2)

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የእመቤታችንን መዋዕለ ጾም አስመልክቶ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለ2005 ዓ.ም. ቅድስት ድንግል ማርያም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የመቀሌ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ያሠለጠናቸውን ደቀ መዛሙርት በዲግሪና በዲፕሎማ አስመረቀ ፡፡

ተመራቂ ደቀ መዛሙርት በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ገለፁ ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በመደበኛውና በማታው መርሐ ግብር በዲግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 64 ደቀ መዛሙርት አስመርቋል ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት በዲፕሎማ መርሐ ግብር አስመረቀ ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቀንና በማታው መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 200 ደቀ መዛሙርት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስመርቀዋል፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ወጣቶች በሀገራቸው እየተከናወነ ያለውን ልማት በማፋጠን የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ገለፁ ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ይህን የገለፁት በደቡብ ክልል ዞኖችና በጋምቤላ ባደረጉት የ3 ቀን ሐዋርያዊ ጉዞ ነው ፡፡

ለሙሉ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የኢትዮጵያ ተወካይ ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚስተር ዩጂን ኦውሱ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ተወካይ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ቅዱስነታቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ለቤተ ክርስቲያን የልማት ተቋሞችዋ ሲያበረክቱት የቆዩትን አስተዋጽኦ በማድነቅ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማዕከልን በማቋቋምና እስካሁን ድረስ ባለሞያ እንዲመደብ በማድረግ ላይ የሚገኙት እገዛዎች ታላቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ወደ ገፅ 1 2 3 >>